የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? በሚለው ትራክት አማካኝነት ጉባኤው የአገልግሎት ክልሉን ለመሸፈን ምን ጥረት እንዳደረገ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሰጠውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ። በርካታ አስፋፊዎች የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት ንቁ! መጽሔቶችን ሲያበረክቱ ስለቆዩ፣ አድማጮች መጽሔቶቹን ጥሩ ውጤት በሚያስገኝ መንገድ ለማበርከት ምን ዓይነት አቀራረብ እንደተጠቀሙ እንዲናገሩ ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ የፍቅርና የልግስና መንፈስ አዳብሩ። በኅዳር 15, 2008 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 6-7 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ፦ “ለሌሎች የምናካፍለው ውድ ሀብት አለን።”* በአንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ አድማጮች ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲሳቡ ስላደረጓቸው ወይም ከተጠመቁ በኋላ ይበልጥ ስለተገነዘቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 19 (43)
ኅዳር 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 79 (177)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን።*
20 ደቂቃ፦ “አስተማሪ መሆን ትችላለህ!”* የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት የሚያስችል ብቃት የለኝም የሚለውን ስሜት ላሸነፈ አንድ አስፋፊ ወይም አቅኚ ቃለ ምልልስ አድርግ። እርዳታ ለማግኘት በይሖዋ የተማመነው እንዴት ነው? ብቁ መሆን እንዲችል ከድርጅቱ በምን በምን መንገዶች እርዳታ አግኝቷል? መጽሐፍ ቅዱስን በማስጠናቱ ሥራ በመካፈሉ ምን በረከቶች አግኝቷል?
መዝሙር 60 (143)
ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን የምስጋና ደብዳቤ አንብብ። በታኅሣሥ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
15 ደቂቃ፦ የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። መጽሔቶቹን በአጭሩ ካስተዋወቅህ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ይበልጥ ሊማርኩ ይችላሉ የሚሏቸውን ርዕሶች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። በመጽሔቱ ውስጥ ያሉትን ርዕሶች ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎችን እና የትኞቹን ጥቅሶች መጠቀም ይቻላል? በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የናሙና አቀራረብ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ለክልሉ ተስማሚ በሆነ አንድ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀውን አጭር መግቢያ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
መዝሙር 83 (187)
ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 (114)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ክልላችሁ የተገኙ ተሞክሮዎች። እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? በሚለው ትራክት አማካኝነት ከጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ምን ያህሉ እንደተሸፈነ ለጉባኤው ተናገር። ትራክቱን ሲያሰራጩ ወይም በትራክቱ ተጠቅመው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ሲሞክሩ ያገኙት ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። በተጨማሪም በኅዳር ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ በሚያበረክቱበት ወቅት የተገኙ አበረታች ተሞክሮዎችን ተናገር። አንድ ወይም ሁለት ግሩም ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “አዲሶች የሚያጋጥማቸውን ተቃውሞ እንዲቋቋሙ አዘጋጇቸው።”* በአንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ በማመራመር መጽሐፍ ላይ “የይሖዋ ምሥክሮች” በሚለው ርዕስ ሥር የሚገኘው ሐሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው በአሳቢነት ተነሳስተው ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንዲችሉ የሚረዳቸው እንዴት እንደሆነ ተነጋገሩበት።
መዝሙር 44 (105)
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።