የካቲት 2 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 21-24
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 22:1-18
ቁ. 2፦ “ልጄ ይህ ነው” (lr ምዕ. 5)
ቁ. 3፦ ለሌሎች ያለንን ፍቅር ማስፋት የምንችልባቸው መንገዶች (2 ቆሮ. 6:11-13)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 98 (220)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ውይይት የሚያስቆም ሐሳብ የሚሰነዝሩ ሰዎች። መግቢያህን በአጭሩ ካቀረብክ በኋላ በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ውይይት ለማስቆም ሲሉ ለሚሰነዝሯቸው በጣም የተለመዱ ሐሳቦች ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 15-20 ተጠቅመን እንዴት መልስ መስጠት እንደምንችል ግለጽ፤ ከዚያም አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት የሌላቸውን ሰዎች እርዱ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 63-67 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በሚመለከት ለሚያነሷቸው የተለያዩ የተቃውሞ ሐሳቦች እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል ተወያዩበት። በክልላችሁ ውስጥ ለተለመደ አንድ የተቃውሞ ሐሳብ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 21 (46)