መጋቢት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 80 (180)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 36-39
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 39:1-16
ቁ. 2፦ ከእኛ በላይ የሆኑ አሉ (lr ምዕ. 8)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆችን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው (rs ገጽ 155 አን. 1 እስከ ገጽ 156 አን. 1)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 23 (48)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የአምላክን ስም ማሳወቅ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 273-274 ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ ደም መውሰድን አስመልክቶ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጠት። ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 73 እስከ 75 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንድ አቅኚ ደም መውሰድን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ የማመራመር መጽሐፍን ተጠቅሞ መልስ ሲሰጥ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በመጋቢት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። የሚበረከተውን ጽሑፍ ይዘት በአጭሩ ከልስ። አድማጮች ጽሑፉን ለማበርከት ምን ጥያቄዎችን ለማንሳትና የትኛውን ጥቅስ ለማንበብ እንዳሰቡ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 96 (215)