ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሚያዝያና ግንቦት፦ መጽሔቶች፤ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? እና ሐምሌ፦ ብሮሹሮች።
◼ በ2009 በዓለም ዙሪያ የሚደረጉትን የአውራጃና የብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ለማስተዋወቅ ብርቱ ጥረት ይደረጋል። በዚህ ጊዜ አስፋፊዎች ልዩ የመጋበዣ ወረቀቶችን በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ ማሰራጨት የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራቸዋል። ዘመቻው የሚጀምረው ጉባኤው የአውራጃ ስብሰባውን ለማድረግ ሦስት ሳምንት ሲቀረው ነው።
◼ ሁሉም አስፋፊዎች የአውራጃ ስብሰባ ባጅ በጉባኤያቸው በኩል ይደርሳቸዋል። የአውራጃ ስብሰባ ልዑካን የሚጠቀሙበት ባጅም ተመሳሳይ ነው።