የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በታኅሣሥ ወር 2008 ባደረግነው እንቅስቃሴ 8,462 አዲስ የአስፋፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ማግኘታችን በጣም ያስደስተናል፤ በዚህ ወር ብቻ 100 አስፋፊዎች የተገኙ ሲሆን ከታኅሣሥ 2007 ጋር ሲወዳደር ከ5 በመቶ በላይ ጭማሪ ያሳያል። ሁላችንም አዘውታሪ ለመሆንና አዲሶች ይሖዋን ማወደስ እንዲጀምሩ ለመርዳት የታሰበበት ጥረት የምናደርግ ከሆነ፣ የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን በምናደርገው በዚህ ልዩ የዘመቻ ወቅትም ሆነ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን በምናደርገው እንቅስቃሴ ተጨማሪ እድገት እንደምናገኝ እንተማመናለን። በአሁኑ ጊዜ 6,045 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያሉን መሆኑ ሌሎች ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ በማስተማር ረገድ ጥሩ እድገት እየተገኘ መሆኑን ይጠቁማል። በመልካም ሥራ መትጋታችሁን ቀጥሉ!