መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“አንዳንድ ሰዎች ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል የሚል እምነት አላቸው፤ ሌሎች ደግሞ የወደፊት ሕይወታችን አሁን በምናደርገው ነገር ላይ የተመካ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን አስተያየት አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጥቅስ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [መክብብ 9:11ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ‘ዕድላችን አስቀድሞ ተወስኗል?’ ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።” በገጽ 26 ላይ ያለውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሚያዝያ 2009
ብዙ ትዳሮች አንደኛው የትዳር ጓደኛ ታማኝነት በማጉደሉ ምክንያት በፍቺ ያከትማሉ። ባለትዳሮች የሚከተለውን ጥቅስ ተግባራዊ ማድረጋቸው ትዳራቸው ዘላቂ እንዲሆን የሚረዳ ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 5:28ን አንብብ። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ ባለትዳሮች ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ሊረዳቸው የሚችል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ይዟል።” በገጽ 28 ላይ የሚጀምረውን ርዕሰ ትምህርት አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“አንድ ሰው በአምላክ ላይ እምነት እንዳያዳብር እንቅፋት የሚሆንበት ነገር ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው ከሆነ እምነት አስፈላጊ ነው። [ዕብራውያን 11:6ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጠንካራ እምነት ለማዳበር የሚረዱንን አራት ነጥቦች ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት 2009
“ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሰዎች መድኃኒቶችን አላግባብ ይጠቀማሉ። ለዚህ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በተለይ ልጆች መድኃኒቶችን አላግባብ እንዲወስዱ የሚያነሳሳቸውን ዋነኛ ምክንያት ይጠቁማል። [ምሳሌ 13:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እንደ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ከመጣው ከዚህ ችግር ራስዎንም ሆነ ቤተሰብዎን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ይናገራል።”