የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. በዘፀአት 23:19 ላይ ከሚገኘው ሕግ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? [w06 4/1 ገጽ 31 አን. 1-5]
2. ኡሪምና ቱሚም የሚባሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? በጥንቷ እስራኤል ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩትስ እንዴት ነው? (ዘፀ. 28:30) [w06 1/15 ገጽ 18፤ w01 9/1 ገጽ 27]
3. ይሖዋ ከሙሴ ጋር “ፊት ለፊት” ይነጋገር የነበረው እንዴት ነው? (ዘፀ. 33:11, 20) [w04 3/15 ገጽ 27]
4. የመገናኛውን ድንኳን ለመገንባት ንብረታቸውንም ሆነ ችሎታቸውን በልግስና ከሰጡት እስራኤላውያን ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘፀ. 35:5, 10) [w99 11/1 ገጽ 31 አን. 1-2]
5. በዘፀአት 40:28 ላይ የተጠቀሰው መጋረጃ በታላቁ የአምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ውስጥ ምንን ያመለክታል? [w00 1/15 ገጽ 15 አን. 7-8]
6. ጥንት በመሠዊያ ላይ ሙሉ በሙሉ ይቀርብ የነበረው “የሚቃጠል መሥዋዕት” የኢየሱስን መሥዋዕት በተመለከተ ምን ነገር ያስገነዝበናል? (ዘሌ. 1:13) [w04 5/15 ገጽ 21 አን. 3]
7. ‘ሥብ ሁሉ የይሖዋ ነው’ የሚለው ትእዛዝ ምን ያስገነዝበናል? (ዘሌ. 3:16, 17) [w04 5/15 ገጽ 22 አን. 2]
8. ለቅድስና ከሚሆነው አውራ በግ ደም ላይ ጥቂት ተወስዶ የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ቀኝ ጆሮ፣ ቀኝ እጅና ቀኝ እግር መቀባቱ ምን ያመለክታል? (ዘሌ. 8:23, 24) [it-2 ገጽ 1113 አን. 4]
9. ዘሌዋውያን 12:8 ስለ ኢየሱስ ወላጆች ምን እንድናስተውል ይረዳናል? ከዚህስ ምን ትምህርት እናገኛለን? [w98 12/15 ገጽ 6 አን. 5]
10. የኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት የሚያከናውነው ተግባር በዓመታዊው የስርየት ቀን በምሳሌያዊ ሁኔታ የተገለጸው እንዴት ነው? (ዘሌ. 16:11-16) [w98 2/15 ገጽ 12 አን. 2]