መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ብዙዎች ያምናሉ። እርስዎስ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምድር ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [መዝሙር 37:11, 29ን አንብብ።] የሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ ያላቸውን የወደፊት ተስፋ አስመልክቶ ኢየሱስ ምን ብሎ እንዳስተማረ ይህ ርዕስ ያብራራል።” በገጽ 22 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ነሐሴ 2009
“የወላጅ ሞትን ያህል በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም አሳዛኝ ሁኔታ የለም ማለት ይቻላል። እርስዎስ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች እንዲህ ካሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መጽናኛ አግኝተዋል። [ራእይ 21:4ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት ሰዎች በተለይም ወጣቶች የሚያጋጥማቸውን የስሜት መለዋወጥ እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ ያብራራል።” በገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“አምላክ ለሚያገለግሉት ሰዎች ሀብት በመስጠት እንደሚባርካቸው ድሆች ግን የአምላክ ሞገስ እንደሌላቸው አንዳንዶች ሲናገሩ ይሰማል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የሚገርመው ነገር ኢየሱስ ሀብታም አልነበረም። [ሉቃስ 9:58ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ አገልጋዮቹን ምን ዓይነት ሀብት በመስጠት እንደሚባርካቸው ይገልጻል።”
ንቁ! መስከረም 2009
“በአሁኑ ጊዜ ያሉ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ቀደም ባሉት ዘመናት ከነበሩት ይበልጥ ከባድ እንደሆኑ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም 2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወላጆችም ሆኑ ወጣቶች እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች ለመቋቋም የሚያስችሏቸው ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ይዟል።”