ጥቅምት 26 የሚጀምር ሳምንት
ጥቅምት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 88 (200)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ከገጽ 209-211 የሚገኘው ተጨማሪ መረጃ
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 11-13
የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 31 (67)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በንግግር የሚቀርብ። በቅርብ የደረሷችሁን መጽሔቶች ይዘት ተናገርና በመጽሔቶቹ ውስጥ ከሚገኙት ርዕሶች መካከል በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሊማርኩ የሚችሉት የትኞቹ እንደሆኑ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንድ ወላጅ ልጁ ለአገልግሎት ዝግጅት እንዲያደርግ ሲረዳው የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ይህ ወላጅ ከልጁ ጋር አንድ ርዕስ ይመርጣሉ፣ ለመግቢያ የሚሆን ጥያቄ ያዘጋጃሉ፤ ከዚያም የሚያነቡትን አንድ ጥቅስ ይመርጣሉ። በመጨረሻም ልጁ የተዘጋጀበትን አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ ያቀርብና ሥራውን በገንዘብ ለመደገፍ የተደረገውን ዝግጅት ይገልጻል።
10 ደቂቃ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመጽሐፉ ውስጥ ከሚገኙት ምዕራፎች መካከል በክልላቸው ውስጥ ለማስተዋወቅ ይበልጥ ውጤታማ ሆነው ያገኟቸው ምዕራፎች የትኞቹ እንደሆኑ አድማጮችን ጠይቅ። መጽሐፉን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ጠየቁ? የትኛውን ሥዕል አሳዩ? እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ አነበቡ? አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንቀጹ ውስጥ የሚገኙትን ጥቅሶች ሁሉ አንብባችሁ ተወያዩባቸው።
መዝሙር 32 (70)