የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 26, 2009 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ይሖዋ፣ በለዓም ከባላቅ ሰዎች ጋር እንዲሄድ ከነገረው በኋላ በለዓም ከሰዎቹ ጋር ሲሄድ የተቆጣው ለምን ነበር? (ዘኍ. 22:20-22) [w04 8/1 ገጽ 27 አን. 3]
2. ፊንሐስ ለይሖዋ ‘መቅናቱ’ ራሳችንን ለይሖዋ መወሰናችንን በሚመለከት ቆም ብለን እንድናስብ የሚረዳን እንዴት ነው? (ዘኍ. 25:11) [w95 3/1 ገጽ 17 አን. 13]
3. ኢያሱ የሙሴ ተተኪ ሆኖ የተመረጠው ለምን ነበር? (ዘኍ. 27:15-19) [w02 12/1 ገጽ 12 አን. 1]
4. ዘኍልቍ 31:27 በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችን ሊያበረታታ የሚችለው እንዴት ነው? [w05 3/15 ገጽ 24]
5. የመማፀኛ ከተሞች መቋቋማቸው ለእስራኤል ሕዝብ ጥቅም ያስገኘው እንዴት ነው? (ዘኍ. 35:11, 12) [w95 11/15 ገጽ 14 አን. 17]
6. ማስተዋል አስፈላጊ የሆነ ክርስቲያናዊ ባሕርይ ነው የምንለው ለምንድን ነው? ምን ጥቅሞችስ ያስገኛል? (ዘዳ. 1:13) [w03 1/15 30፤ w00 10/1 ገጽ 32 አን. 1-3]
7. የሙሴ ሕግ የአምላክን ጽድቅ የገለጸው በምን መንገዶች ነው? (ዘዳ. 4:8) [w02 6/1 ከገጽ 14 አን. 8 እስከ ገጽ 15 አን. 9-10]
8. ከዘዳግም 6:16-18 አንጻር ይሖዋን የምንፈትንበት ትክክለኛ የሆነው መንገድ እና የተሳሳተው መንገድ የትኛው እንደሆነ ግለጽ። [w04 9/15 ገጽ 26 አን. 6]
9. ይሖዋ የተናገራቸው ቃላት የእስራኤላውያንን መሠረታዊ ፍላጎት ያሟሉት እንዴት ነው? እነዚህ ቃላት በዛሬው ጊዜ እኛን የሚመግቡን እንዴት ነው? (ዘዳ. 8:3) [w99 8/15 ገጽ 25-26]
10. በዘዳግም 12:16, 24 ላይ ያለው መሠረታዊ ሥርዓት የራሳችንን ደም በመጠቀም ስለሚከናወኑ የሕክምና ዘዴዎች ያለንን አመለካከት የሚነካው እንዴት ነው? [w00 10/15 ገጽ 30 አን. 7]