የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/09 ገጽ 4
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 12/09 ገጽ 4

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ታኅሣሥ፦ ታላቅ ሰው ወይም ከታላቁ አስተማሪ ተማር፤ ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?

◼ ለ2010 የመታሰቢያ በዓል የሚያገለግል የመጋበዣ ወረቀት እያንዳንዱ ጉባኤ በሚመራበት ቋንቋ በቅርቡ ይላካል። በክልላችሁ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ካሉና በዚህ ቋንቋ የተዘጋጀ የመጋበዣ ወረቀት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) መጠየቅ አለባችሁ።

◼ ብዙ አስፋፊዎች ሰዎች በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ ማለትም በመንገድ ላይ፣ በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እንዲሁም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው በሌሎች ቦታዎች በመመሥከር ግሩም ውጤቶች አግኝተዋል። ይህ የሚያስመሰግን ቢሆንም ግሩም ምሥክርነት የምንሰጠው በአንደበታችን ብቻ መሆን አይኖርበትም፤ ምክንያታዊ መሆናችንም በጣም አስፈላጊ ነው። በንግድ አካባቢዎችና በአውራ ጎዳናዎች ወይም በመናፈሻዎች ውስጥ የሚዘዋወሩ ሰዎችን አሊያም በንግድ ሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞችን አሁንም አሁንም አነጋግረን እንዳናሰለቻቸው በእያንዳንዱ ጉባኤ ውስጥ ያሉ አስፋፊዎች የአገልግሎት ክልል ወሰናቸውን ማክበር ይኖርባቸዋል። አገልግሎታችንን ሥርዓትና ክብር ባለው መንገድ ማከናወን እንድንችል በጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል ሌላ ጉባኤ መርዳት የምንችልበት ዝግጅት እስካልተደረገልን ድረስ በጉባኤያችን የአገልግሎት ክልል ውስጥ ብቻ መሥራት ይኖርብናል። ይህ ደግሞ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች በሚጠቀሙበት የመንግሥት አዳራሽ አካባቢ የሚገኘውን የአገልግሎት ክልል ወሰን ማክበርን ይጨምራል፤ በመንግሥት አዳራሹ አካባቢ ማገልገል ያለበት አዳራሹ የሚገኝበት ክልል ባለቤት የሆነው ጉባኤ ብቻ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ