የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ሐምሌና ነሐሴ በበርካታ አካባቢዎች የዝናብ ወራት ቢሆኑም ይሖዋን በማወደስ ረገድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነበር። በሐምሌ ወር በአገራችን 6,573 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ተመርተዋል፤ ይህ ቁጥር በአገራችን ከተመዘገበው ታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ሲሆን ወደፊት ተጨማሪ እድገት እንደምናደርግ ይጠቁማል። በነሐሴ ወር ደግሞ 8,672 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ማግኘታችን አስደስቶናል፤ በዓመቱ ውስጥ በአጠቃላይ 4.4 በመቶ ጭማሪ አግኝተናል።