የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 28, 2009 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ክርስቲያኖች በዘዳግም 14:1 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት በዛሬው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉት እንዴት ነው? [w05 1/1 ገጽ 28፤ w04 9/15 ገጽ 27 አን. 4]
2. በዘዳግም 20:5-7 ላይ የሚገኘው ሐሳብ መሠረታዊ ሥርዓት በዛሬው ጊዜ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? [w04 9/15 ገጽ 27 አን. 5]
3. እስራኤላውያን ከጦርነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከሌሎች ብሔራት የተለዩ የነበሩት እንዴት ነው? (ዘዳ. 20:10-15, 19, 20፤ 21:10-13) [cl ከገጽ 134-135 አን. 17]
4. ይሖዋን ከልብ በመነጨ ደስታ እንድናገለግለው ምን ሊረዳን ይችላል? (ዘዳ. 28:47) [w95 1/15 ገጽ 16 ከአን. 4-5]
5. ወላጆች፣ ይሖዋ ለእስራኤል የነበረውን ፍቅር ከሚገልጸው በዘዳግም 32:9, 11, 12 ላይ ከተሰጠው ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? [w01 10/1 ገጽ 9 ከአን. 7-9]
6. ሰላዮቹን ይከታተሉ የነበሩትን የንጉሡን መልእክተኞች ለማሳሳት ረዓብ የተጠቀመችባቸውን የማታለያ ቃላት ልንረዳቸው የሚገባው እንዴት ነው? (ኢያሱ 2:4, 5) [w93 12/15 ገጽ 25 አን. 1]
7. በኢያሱ 3:15, 16 ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘው የእስራኤላውያን ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን? [w04 12/1 ገጽ 9 አን. 5]
8. ኢያሱ የአካንን ስርቆት በማጋለጥ ከወሰደው እርምጃ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ኢያሱ 7:20-25) [w04 12/1 ገጽ 11 አን. 4]
9. ኢያሱ 9:22, 23 የአምላክ ቃል ሳይፈጸም እንደማይቀር የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? [w04 12/1 ገጽ 11 አን. 3፤ si ገጽ 44 አን. 13]
10. ከካሌብ ታሪክ ምን የሚያበረታታ ሐሳብ ማግኘት እንችላለን? (ኢያሱ 14:8, 10-12) [w04 12/1 ገጽ 12 አን. 2፤ w93 5/15 ገጽ 29 አን. 1]