የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ረዓብ በእምነት በሠራችው ሥራ ጻድቅ ሆና ተቆጠረች
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ታኅሣሥ 15
    • ድል እንዲገኝ ማድረጉ ሰላዮቹ የብልግና ድርጊት አለመፈጸማቸውን ያረጋግጣሉ። — ዘሌዋውያን 18:​24–30

      ሰላዮቹን ይከታተሉ የነበሩትን ሰዎች ለማሳሳት ረዓብ የተጠቀመችባቸው የማታለያ ቃላትስ እንዴት ይታያሉ? አምላክ ያደረገችውን ተቀብሎታል። (ከሮሜ 14:​4 ጋር አወዳድር።) የአምላክን አገልጋዮች ከሞት ለማዳን የራሷን ሕይወት አደጋ ላይ ጥላለች። ሌሎችን ለመጉዳት ታስቦ የሚነገር ውሸት በይሖዋ ዓይን መጥፎ ቢሆንም ማንም ሰው ለማይመለከታቸው ሰዎች እውነተኛ መረጃዎችን የመንገር ግዴታ የለበትም። ኢየሱስ ክርስቶስም ቢሆን የማያስፈልግ ጉዳት እንዳይደርስበት ዝርዝር ነገሮችን ወይም ቀጥተኛ መልስ ያልተናገረበት ጊዜ አለ። (ማቴዎስ 7:​6፤ 15:​1–6፤ 21:​23–27፤ ዮሐንስ 7:​3–10) ረዓብም ጠላት የሆኑትን ባለ ሥልጣኖች ማሳሳቷ በዚሁ ዓይን ሊታይ እንደሚችል ግልጽ ነው።

      ረዓብ ያገኘችው ሽልማት

      ረዓብ እምነት በማሳየቷ ምን ሽልማት አገኘች? በኢያሪኮ ላይ ከደረሰው ጥፋት መትረፏ ከይሖዋ ያገኘችው በረከት መሆኑ እርግጠኛ ነገር ነው። በኋላም ከይሁዳ ነገድ የሆነውንና የምድረበዳ አለቃ የነበረውን የነአሶንን ልጅ ሳልሞንን (ሳልማን) አገባች። ሳልሞንና ረዓብ አምላካዊ ሰው የነበረውን ቦኤዝን ወለዱና ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ዳዊት የሚያደርስ የዘር መስመር አስገኙ። (1 ዜና መዋዕል 2:​3–15፤ ሩት 4:​20–22) ከዚህ የበለጠ ግምት የሚሰጠው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ በሚናገረው የማቴዎስ ጽሑፍ ላይ በስም ከተጠቀሱት አራት ሴቶች መካከል አንዷ የቀድሞዋ ጋለሞታ ረዓብ መሆኗ ነው። (ማቴዎስ 1:​5, 6) ከይሖዋ እንዴት ያለ ታላቅ ብድራት አግኝታለች!

      ረዓብ እስራኤላዊ ያልሆነችና ጋለሞታ የነበረች ሴት ብትሆንም አንኳ በይሖዋ ላይ ሙሉ እምነት ያላት መሆኗን በሥራዋ ያሳየች እጅግ በጣም ግሩም ምሳሌ የሆነች ሴት ነች። (ዕብራውያን 11:​30, 31) የግልሙትናን ኑሮ እንደተዉት እንደ አንዳንዶቹ ሴቶች ትንሣኤ በማግኘት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የመኖር ሌላ ሽልማት ታገኛለች። (ሉቃስ 23:​43) ረዓብ በሥራ በተደገፈው እምነትዋ ምክንያት በአፍቃሪውና በመሐሪው ሰማያዊ አባታችን ዘንድ ተቀባይነት አግኝታለች። (መዝሙር 130:​3, 4) የእርስዋ መልካም ምሳሌ የጽድቅ አፍቃሪዎች የሆኑ ሁሉ ይሖዋ አምላክ የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንዲያደርጉ ማበረታቻ እንደሚሰጥ የተረጋገጠ ነው።

  • ዓይናችን “ጤናማ” ሆኖ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ታኅሣሥ 15
    • ዓይናችን “ጤናማ” ሆኖ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ

      ላይቤሪያን ወይም በአሜሪካን አገር የሚገኘውን ተነሲ የተባለውን ክፍለ ሀገር የሚያክለው ጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ (ጂ ዲ አር) ወይም ምሥራቅ ጀርመን በመባል ይታወቅ የነበረው አገር ጥቅምት 3, 1990 ምዕራብ ጀርመን ተብሎ ይጠራ ከነበረው አገር ጋር ተቀላቀለ።

      የሁለቱ ጀርመኖች መዋሀድ ብዙ ለውጦችን አስከትሏል። ሁለቱን አገሮች አለያይቷቸው የነበረው የግንቡ አጥር ብቻ ሳይሆን የርዕዮተ ዓለም ድንበር ጭምር ነበር። ይህ ለውጥ በዚያ አገር የሚኖሩትን ሰዎች አኗኗር እንዴት ነክቷል? በዚያ አገር የሚኖሩ የይሖዋ ምስክሮች ኑሮ ላይ ምን ዓይነት ለውጥ አስከትሏል?

      ለውህደቱ ምክንያት የሆነውና በ1989 የተጀመረው ቬንደ የተባለ አብዮት ለአርባ ዓመታት የቆየውን የሶሺያሊዝም አገዛዝ ተከትሎ የመጣ ነበር። በእነዚህ አርባ ዓመታት የይሖዋ ምስክሮች ሥራ ታግዶ ነበር። በጣም የተፋፋመ ስደት ይደርስባቸው

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ