መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“የገና በዓል በሚከበርበት በዚህ ወቅት ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ልደት የሚናገረውን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ በሥዕል ለመግለጽ ይሞክራሉ። [ማቴዎስ 2:1, 11ን አንብብ።] ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በአብዛኛው በሥዕል ከሚገለጸው የተለየ እንደሆነ አስተዋሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕሰ ትምህርት በዚያን ጊዜ በእርግጥ ምን እንደተከናወነ ያብራራል።” በገጽ 31 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ታኅሣሥ 2009
“ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ ስለተናገረው ሐሳብ ምን እንደሚሰማዎት ቢነግሩኝ ደስ ይለኛል። [ማቴዎስ 5:3ን አንብብ።] በዛሬው ጊዜ በጣም ብዙ ሃይማኖቶች ስላሉ መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ለማርካት የምንመርጠው ሃይማኖት ልዩነት የሚያመጣ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ እውነተኛ መንፈሳዊ እርካታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ይዟል።” በገጽ 12 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“የአልኮል መጠጥ መጠጣትን በተመለከተ እርስ በርስ የሚጋጩ ሃይማኖታዊ ሐሳቦች ይሰነዘራሉ። በዚህ ረገድ የአምላክ አመለካከት ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ በአንድ ወቅት ኢየሱስ በተአምር ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ እንደቀየረ ቢናገርም ሌላ ትኩረት የሚስብ ሐሳብም ይዟል። [ምሳሌ 23:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2010
“በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ፣ ብዙ ሰዎች ከአቅማቸው በላይ እንደሚሠሩና ውጥረት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። እርስዎስ እንዲህ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህን ምክንያታዊ የሆነ ምክር ልብ ይበሉ። [መክብብ 4:6ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለሥራ፣ ለቤተሰብና ለመዝናኛ የምናውለውን ጊዜ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማመጣጠን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል። ለሥራ ፈላጊዎች የሚሆን ሐሳብም ይዟል።”