ግንቦት 17 የሚጀምር ሳምንት
ግንቦት 17 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 13 አን. 5-15፤ በገጽ 150 የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 9-12
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 10:1-12
ቁ. 2፦ ኢየሱስ የሚያስተምረው ትምህርት በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ እንዲመሠረት ያደረገው ለምንድን ነው? (ዮሐ. 7:16-18)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ለአምልኮ የሚያገለግሉ ምስሎችን ስለ መሥራት ምን ይላል? (rs ከገጽ 183 አን. 3 እስከ ገጽ 184 አን. 3)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በእረፍት ጊዜህ ረዳት አቅኚ መሆን ትችላለህ? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ረዳት አቅኚ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች በመግለጽ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 112-113 ያለውን ሐሳብ በአጭሩ ከልስ። በዓመት እረፍታቸው ወይም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ረዳት አቅኚ የሆኑ አስፋፊዎች ያገኙትን በረከት እንዲናገሩ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች—መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 101 አን. 2 እስከ ገጽ 102 አን. 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነትን አስመልክቶ በአካባቢያችሁ የተገኘ አንድ ወይም ሁለት ግሩም ተሞክሮ ተናገር ወይም በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ክርስቲያን አገልጋዮች መጸለይ ያስፈልጋቸዋል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።