ግንቦት 24 የሚጀምር ሳምንት
ግንቦት 24 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 13 አን. 16-26፤ በገጽ 156 የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 13-15
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 13:23-33
ቁ. 2፦ ምስሎች እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ የሚረዱ መሣሪያዎች ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ? (rs ገጽ 184 አን. 4-8)
ቁ. 3፦ ዓለምን ሙሉ በሙሉ ልንጠቀምበት የማይገባን ለምንድን ነው? (1 ቆሮ. 7:31)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በሰኔ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ከልስ። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሰ ትምህርቶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ተጠቅሞ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ጥሩ አቅኚ ሊወጣህ ይችላል!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።