ሐምሌ 26 የሚጀምር ሳምንት
ሐምሌ 26 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 16 አን. 15-22፣ በገጽ 194 ላይ የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 15-17
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት 15:1-15
ቁ. 2፦ ሰዎች የአምላክን ትእዛዞች ቸል በማለት በራሳቸው ተመርተው ያሻቸውን ለመወሰን እንዲፈልጉ የገፋፋቸው ማን ነው? (rs ገጽ 190 አን. 1-2)
ቁ. 3፦ አርማጌዶን መምጣቱ አስፈላጊ የሆነው ለምድን ነው?
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች—ክፍል 3። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 114 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 115 አንቀጽ 3 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በጉባኤ ውስጥ ላሉ በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ወይም በጊልያድ ትምህርት ቤት ለሠለጠኑ ምሳሌ የሚሆኑ አስፋፊዎች ሥልጠናው እንዴት እንደጠቀማቸው ቃለ ምልልስ አድርግ። በጉባኤው ውስጥ ሥልጠናውን ያገኙ አስፋፊዎች ከሌሉ ከጽሑፎች ላይ የተገኙ ተሞክሮዎች ተናገር።
10 ደቂቃ፦ በነሐሴ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ጥበብ ጻድቅ መሆኗ በሥራዋ ተረጋግጧል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።