የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 30, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከሐምሌ 5 እስከ ነሐሴ 30, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ሰለሞን በቤተ መቅደሱ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ወቅት ባቀረበው ጸሎት ላይ ማሰላሰላችን ስለ ይሖዋ ባሕርያት ያለንን አድናቆት ከፍ የሚያደርግልን እንዴት ነው? (1 ነገ. 8:22-53) [w05 7/1 ገጽ 30 አን. 3]
2. ዳዊት ብዙ ስህተቶችን ሠርቶ ሳለ ከይሖዋ ጋር “በልበ ቅንነት” ሄዷል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (1 ነገ. 9:4) [w97 5/1 ገጽ 5 አን. 1-2]
3. ንግሥተ ሳባ ሰለሞንን አስመልክታ ስትናገር “ሁል ጊዜ በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙ ሹማምትህስ እንዴት የታደሉ [“ደስተኞች፣” NW] ናቸው!” ያለችው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 10:4-8) [w99 11/1 ገጽ 20 አን. 5-7]
4. አብያ በወግ በማዕረግ እንዲቀበር ይሖዋ ማዘዙ ምን ትምህርት ይሰጠናል? (1 ነገ. 14:13) [cl ገጽ 244 አን. 11]
5. ኤልያስ ለመጀመሪያ ጊዜ አክዓብን ለማነጋገር የሄደው ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ ነበር የምንለው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 17:1) [w08 4/1 ገጽ 19፣ ሣጥኑ]
6. ኤልያስ ‘በሁለት ሐሳብ ትዋልላላችሁ’ ሲል ምን ማለቱ ነበር? (1 ነገ. 18:21) [w08 1/1 ገጽ 19 አን. 2-3]
7. በኤልያስ ሁኔታ እንደታየው ይሖዋ ከአገልጋዩቹ ጋር በተያያዘ ኃይሉን የሚጠቀምበት ለምን ዓላማ ነው? (1 ነገ. 19:1-12) [cl ገጽ 42-43 አን. 15-16]
8. ናቡቴ የወይን ተክል ቦታውን ለአክዓብ ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነው ለምንድን ነው? ከዚህ ሁኔታስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ነገ. 21:3) [w97 8/1 ገጽ 13 አን. 18-20]
9. በሱነም ትኖር የነበረችው ሴት ለኤልሳዕ ስትል ‘የተቸገረችው’ ወይም መሥዋዕትነት የከፈለችው እንዴት ነው? (2 ነገ. 4:13) [w97 10/1 ገጽ 30 አን. 6-8]
10. ኤልሳዕ የንዕማንን ስጦታ ያልተቀበለው ለምንድን ነው? (2 ነገ. 5:15, 16) [w05 8/1 ገጽ 9 አን. 2]