የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 25, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 6 እስከ ጥቅምት 25, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ንጉሥ ዓዛርያስ (ዖዝያን) ያሳለፈውን ሕይወት በመመርመር ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (2 ነገ. 15:1-6) [w91 7/15 ገጽ 29-30፤ w98 11/1 ገጽ 15 አን. 8]
2. በ2 ነገሥት 13:20, 21 ላይ የሚገኘው ዘገባ እንደ ቅዱስ ተደርገው ለሚታዩ ነገሮች ክብር መስጠት እንዳለብን አያሳይም? [w05 8/1 ገጽ 11 አን. 4]
3. በ2 ነገሥት 18:21 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ሕዝቅያስ ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ጥምረት ፈጥሮ እንደነበር ያሳያል? [w05 8/1 ገጽ 11 አን. 6]
4. ይሖዋ ዓላማውን ‘እንዳደረገው’ የተገለጸው ለምንድን ነው? (2 ነገ. 19:25 የ1954 ትርጉም) [w99 8/15 ገጽ 14 አን. 3]
5. ኢዮስያስ የሞተው በጦርነት ሆኖ ሳለ በ2 ነገሥት 22:20 ላይ ሕልዳና የተናገረችው ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (2 ነገ. 23:28-30) [w00 9/15 ገጽ 30 አን. 3]
6. በአንደኛ ሳሙኤል 16:10, 11 ላይ ዳዊት የእሴይ ስምንተኛ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ የተገለጸ ቢሆንም ዕዝራ ሰባተኛ ልጅ አድርጎ የገለጸው ለምንድን ነው? (1 ዜና 2:15) [w02 9/15 ገጽ 31]
7. በጥንት ዘመን የኖሩት ገለዓዳውያን ከተዉልን ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ዜና 5:10, 18-22) [w05 10/1 ገጽ 9 አን. 7]
8. ከሌዋውያኑ የበር ጠባቂዎች ምን ትምህርት እናገኛለን? (1 ዜና 9:26, 27) [w05 10/1 ገጽ 9 አን. 8]
9. የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 300 ሆኖ ሳለ በ2 ሳሙኤል 23:8 ላይ 800 እንደሆነ ተደርጎ የተገለጸው ለምንድን ነው? (1 ዜና 11:11) [w05 10/1 ገጽ 10 አን. 3]
10. በ1 ዜና 13:11 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ዳዊት በሁኔታው ‘ማዘኑ’ ምን ስህተት አለው? [w05 10/1 ገጽ 11]