ኅዳር 1 የሚጀምር ሳምንት
ኅዳር 1 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 16-20
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል 17:1-10
ቁ. 2፦ ሌሎች ሃይማኖቶች መጽሐፍ ቅዱስን ይከተላሉ? (rs ገጽ 204 አን. 4)
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊሸሿቸው የሚገቡ ነገሮችን በተመለከተ ቅዱሳን መጻሕፍት የሚሰጡት ማስጠንቀቂያ
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ተቋቁሞ መጽናት። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 176 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 178 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። ከባድ የጤና ችግር ቢኖርበትም በአገልግሎቱ ቀናተኛ ሆኖ እንዲቀጥል የረዳው ምን እንደሆነ እንዲናገር ለአንድ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በኅዳር ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።