በውጭ አገር ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎች በአስቸኳይ ሲያስፈልጓችሁ
አንዳንድ ጊዜ በውጭ አገር ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎችን ማንበብ የሚፈልጉ ሰዎች ያጋጥሙናል፤ ሆኖም እነዚህ ጽሑፎች በጉባኤያችን አይኖሩ ይሆናል። ኢንተርኔት መጠቀምና ማተም የምትችል ከሆነ ጽሑፎቻችንን ወደ 400 በሚጠጉ ቋንቋዎች ማተም እንደምትችል ታውቃለህ? ይህን ማድረግ የምትችልበት መንገድ ከዚህ በታች ሰፍሯል፦
• www.watchtower.org የሚለውን የይሖዋ ምሥክሮችን ሕጋዊ ድረ ገጽ ክፈት።
• በመነሻው ገጽ (ሆም ፔጅ) ላይ በስተቀኝ በኩል የተወሰኑ ቋንቋዎችን ዝርዝር ታገኛለህ። የሁሉንም ቋንቋዎች ዝርዝር መመልከት ከፈለግህ የዓለም ካርታ ያለበትን ምልክት ተጫን ወይም ክሊክ አድርግ።
• ከዚያም የምትፈልገውን ቋንቋ ተጫን። በዚህ ጊዜ ልታትማቸው የምትችላቸው ትራክቶችን፣ ብሮሹሮችን እና ሌሎች ጽሑፎችን የያዘ ገጽ ይወጣል። ይህ ገጽ በመረጥከው ቋንቋ የተዘጋጀ በመሆኑ የጽሑፎቹን ርዕሶች ማንበብ ባትችል አትጨነቅ።
• የፈለግከውን ጽሑፍ ተጫን። በዚህ ጊዜ ጽሑፉ በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ ስለሚታይ የምትፈልገውን ማተም ትችላለህ።
ድረ ገጻችን የያዘው የተወሰኑ ጽሑፎችን ብቻ ነው፤ በመሆኑም ሌሎች ጽሑፎችን ማግኘት የምንችለው በጉባኤ በኩል ነው። የምናነጋግረውን ሰው ፍላጎት ካየን በኋላ በጽሑፍ ክፍሉ በኩል ጽሑፎችን ማዘዛችን የተሻለ ነው።