የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 27, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 2 እስከ ሰኔ 27, 2011 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ኢዮብ በደል ላደረሱበት ሰዎች እንዲጸልይላቸው ይሖዋ መጠየቁ ለእኛ ምን ትምህርት ይዟል? (ኢዮብ 42:8) [w98 8/15 ገጽ 30 አን. 5]
2. ዛሬ ያሉ ክርስቲያኖች የሚያቀርቧቸው ‘የጽድቅ መሥዋዕቶች’ ምንድን ናቸው? (መዝ. 4:5) [w06 5/15 ገጽ 19 አን. 1]
3. ዳዊትን ኩላሊቶቹ የሚገሥጹት እንዴት ነው? (መዝ. 16:7 የ1954 ትርጉም) [w04 12/1 ገጽ 14 አን. 9]
4. ‘ሰማያት የአምላክን ክብር’ የሚናገሩት እንዴት ነው? (መዝ. 19:1) [w04 10/1 ገጽ 10 አን. 8]
5. መዝሙር 27:14 (NW) በተስፋና በድፍረት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልጸው እንዴት ነው? [w06 10/1 ገጽ 26-27 አን. 3, 6]
6. መዝሙር 37:21 ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት እንዴት ሊነካው ይገባል? [w98 11/15 ገጽ 25 አን. 3፤ w88-E 8/15 ገጽ 17 አን. 8]
7. መንፈሳዊ ነገሮችን ማድነቅን በተመለከተ በግዞት ከነበረ አንድ ሌዋዊ ምን ልንማር እንችላለን? (መዝ. 42:1-3) [w06 6/1 ገጽ 9 አን. 3]
8. ዳዊት በመዝሙር 51:18 ላይ ካቀረበው ጸሎት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? [w06 6/1 ገጽ 11 አን. 1]
9. ዳዊት “በእሽታ መንፈስ” እንዲደገፍ ሲጠይቅ ምን ማለቱ ነበር? (መዝ. 51:12) [w06 6/1 ገጽ 9 አን. 10]
10. በአምላክ ቤት እንዳለ የወይራ ዛፍ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (መዝ. 52:8) [w00 5/15 ገጽ 29 አን. 6]