ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 15 አን. 10-19 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 87-91 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 89:26-52 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ደስተኛ የሆኑባቸው ምክንያቶች (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት ጦርነትንና ምግባረ ብልሹነትን ያስወግዳል—rs ገጽ 229 አን. 2-5 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በዚህ ገጽ ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በነሐሴ ወር የመጀመሪያው ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ ትምህርት አዘል ምሳሌዎችን ተጠቀሙ። የአገልግሎት ትምህርት ቤት በተባለው መጽሐፍ በገጽ 240 እስከ 243 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ለአንድ የቤት ባለቤት ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ አንድን ነጥብ ለማስረዳት ውጤታማ ሆኖ ያገኙትን ምሳሌ በአጭሩ እንዲናገሩ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 54 እና ጸሎት