ነሐሴ 29 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 16 አን. 20-28 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 110-118 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በመስከረም ወር የመጀመሪያው ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። “የግለሰቡን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ የቆዩ መጽሔቶችን ወይም ብሮሹሮችን አበርክቱ” የሚለውን ርዕስ በንግግር አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ በዕድሜ እየገፉ ቢሄዱም ቀናተኞች ናቸው። በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 61 አንቀጽ 1 እና 2፣ ገጽ 67 አንቀጽ 1 እንዲሁም ከገጽ 135 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 136 አንቀጽ 1 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በእያንዳንዱ ተሞክሮ ላይ ውይይት ካደረጋችሁ በኋላ ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ተናገር። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚቻል አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 31 እና ጸሎት