መስከረም 19 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 17 አን. 15-23 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 135-141 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 137:1 እስከ 138:8 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ጳውሎስ በሮም 14:7-9 ላይ የተናገረው ሐሳብ የሚያጽናናን እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋል—rs ገጽ 232 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ከልስ። ለተደረጉት መልካም ነገሮች ጉባኤውን አመስግን። በአገልግሎት ያገኟቸውን ግሩም ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ለአንድ ወይም ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች ጥቀስ፤ ከዚያም ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን ተናገር።
10 ደቂቃ፦ ልታብራራ ትችላለህ? የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 197-198 በጥያቄ 12 እና ጥያቄ 13 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ “ይሖዋ ለዚህ ሥራ ሥልጠና እየሰጠን ነው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት