ኅዳር 28 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ኅዳር 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 2 ከአን. 11-19 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማሕልየ መሓልይ 1-8 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ማሕልየ መሓልይ 1:1-17 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የይሖዋ ምሥክሮች የመጨረሻዎቹ ቀኖች የጀመሩት በ1914 ነው የሚሉት ለምንድን ነው?—rs ገጽ 239 ከአን. 1-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የሌሎችን አክብሮት ማትረፍ የምንችለው እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በታኅሣሥ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “የጥሩ አስተማሪ መለያ ባሕርይ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። መጽሐፍ ቅዱስን ያስጠናቸው ሰው ያሳያቸው ፍቅር መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ በታኅሣሥ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ውስጥ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ አንዳንድ ርዕሶችን መርጠህ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚቻል እንዲናገሩ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎች አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 18 እና ጸሎት