ሰኔ 18 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 29 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 11 ከአን. 1-9 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3-5 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ 5:1-22 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ‘በድንግል ማርያም ታምናላችሁ?’ ብሎ ለሚጠይቅ ሰው መልስ መስጠት—rs ገጽ 260 ከአን. 2-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ መሪነት መጻፉን እንድናምን የሚያደርገን ምንድን ነው?—2 ጢሞ. 3:16 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን። በንግግር የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ታስታውሳለህ? በሚያዝያ 15, 2012 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎች ያላቸው ጠቀሜታ። በ2012 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) በገጽ 92 አንቀጽ 1፣ በገጽ 112 አንቀጽ 3 እንዲሁም በገጽ 113 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
መዝሙር 24 እና ጸሎት