ሰኔ 25 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 11 ከአን. 10-15 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 1-5 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ለደረሰው የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በሐምሌ ወር የመጀመሪያው ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ አገልግሎት ስትወጡ ጊዜያችሁን በጥበብ ተጠቀሙበት። (ኤፌ. 5:15, 16) በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። (1) በሚከተሉት ወቅቶች ጊዜያችንን በጥበብ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? (ሀ) የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ስንመራ፣ (ለ) የስምሪት ስብሰባው ከተደመደመ በኋላ፣ (ሐ) አብሮን የተመደበው ወንድም ፍላጎት ካሳየ ሰው ጋር ረጅም ውይይት ሲያደርግ እንዲሁም (መ) ተራርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ። (2) የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጋችን ጊዜ ላለማባከን የሚረዳን እንዴት ነው? (ሀ) የሚቻል ከሆነ ከስምሪት ስብሰባ በፊት ከቤተሰባችን ጋር መመገባችን (ለ) ሁላችንም ለመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባው በሰዓቱ መድረሳችን (ሐ) ስምሪቱን የሚመራው ወንድም ሰዎችን ሲመድብ በጥሞና ማዳመጣችንና ስብሰባው ካለቀ በኋላ የተመደቡትን ሳያስፈልግ አለመቀያየራችን (መ) ሁሉም ሰው አገልግሎት ከመውጣቱ በፊት ክልሉን ማወቁ።
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። በሐምሌ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ይዘት ከተናገርክ በኋላ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 29 እና ጸሎት