የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 25, 2012 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት ቀን የተገለጸው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. ኤርምያስ ከባድ የኢኮኖሚ ችግር ማሳለፉ ምን ያስተምረናል? (ኤር. 37:21 የ1980 ትርጉም) [ግንቦት 7, w97 9/15 ገጽ 3 አን. 4 እስከ ገጽ 4 አን. 1]
2. ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች የአቤሜሌክን ምሳሌ መኮረጅ የሚችሉት በምን መንገዶች ነው? (ኤር. 38:8-13) [ግንቦት 7, su ገጽ 179 አን. 9]
3. ይሖዋ ታማኞቹን እንደማይጥል ከአቤሜሌክ ታሪክ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ኤር. 39:16-18) [ግንቦት 14, w07 2/1 ገጽ 19 አን. 7]
4. ባሮክ ለራሱ የተመኘው “ታላቅ ነገር” ምን ሊሆን ይችላል? ይሖዋ ሲመክረው ከሰጠው ምላሽስ ምን እንማራለን? (ኤር. 45:5) [ግንቦት 21, w06 8/15 ገጽ 18 አን. 1፤ ገጽ 19 አን. 5]
5. ይሖዋ በባቢሎን ‘ውሆች ላይ ድርቅ’ እንደሚመጣ ያስነገረው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (ኤር. 50:38) [ግንቦት 28, dp ገጽ 150-151 አን. 3]
6. አይሁዳውያን በኤርምያስ 51:6 ላይ የሚገኘውን ትንቢታዊ መልእክት ተግባራዊ ያደረጉት እንዴት ነው? ለእኛስ ምን ትምህርት ይሰጠናል? [ሰኔ 4, w08 6/15 ገጽ 8-9 አን. 9-11]
7. የይሖዋ ‘የእግር መቀመጫ’ እና “ማደሪያ [“ዳስ፣” NW]” ተብለው የተገለጹት ምንድን ናቸው? (ሰቆ. 2:1, 6) [ሰኔ 11, w07 6/1 ገጽ 9 አን. 2]
8. ከባድ ሥቃይ ቢደርስብንም እንኳ መጽናት የምንችለው እንዴት ነው? (ሰቆ. 3:21-26, 28-33) [ሰኔ 18, w07 6/1 ገጽ 11 አን. 3]
9. አንድ ሰው በወጣትነቱ የመከራን ቀንበር መሸከም መማሩ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? (ሰቆ. 3:27) [ሰኔ 18, w07 6/1 ገጽ 11 አን. 4፤ w87-E 2/15 ገጽ 24 አን. 1]
10. ሰዎች ግዴለሽ ቢሆኑም የሕዝቅኤል ምሳሌ በድፍረት እንድንናገር የሚያነሳሳን እንዴት ነው? (ሕዝ. 3:8, 9) [ሰኔ 25, w08 7/15 ገጽ 8 አን. 6-7]