ሐምሌ 2 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 11 ከአን. 16-23 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 6-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሕዝቅኤል 7:14-27 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዮናታን ትሑት በመሆን ረገድ ጥሩ ምሳሌ የተወው እንዴት ነው?—1 ሳሙ. 23:16-18 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ቂጣውና ወይኑ ቃል በቃል ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደምነት ይለወጣል?—rs ከገጽ 261 አን. 1 እስከ ገጽ 262 አን. 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ለምናነጋግረው ሰው ነጥቡን ማስረዳት የምንችልበት መንገድ።—ክፍል 1 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 251 እስከ ገጽ 253 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። ሁለት ወይም ሦስት ርዕሶችን ምረጥና እነዚህ ርዕሶች በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ባለው ሴኮንድ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንደሚቻል እንዲናገሩ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 31 እና ጸሎት