ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 6/15 ከገጽ 17 አን. 8 እስከ ገጽ 19 አን. 12 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘካርያስ 1-8 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘካርያስ 8:1-13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ይሖዋ ሉዓላዊ ገዥያችን እንደሆነ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—መዝ. 73:28 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ከሰብዓዊ ፍልስፍና ይልቅ የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ማጥናት ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዳለን የሚያሳየው ለምንድን ነው?—rs ከገጽ 290 አን. 3 እስከ ገጽ 291 አን. 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ “. . . መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች።” በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ልናውጀው የሚገባ መልእክት—“እግዚአብሔርን ፍራ፣ ትእዛዙንም ጠብቅ።” በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 272 አንስቶ ገጽ 275 ላይ እስከሚገኘው ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ ሞክራችሁታል? በውይይት የሚቀርብ። በቅርቡ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡት በሚከተሉት ርዕሶች ውስጥ የተሰጡትን ሐሳቦች በንግግር መልክ በአጭሩ ከልስ፦ “በንግድ አካባቢዎች በድፍረት መመሥከር” (km 3/12)፣ “ሰዎች አምላክን እንዲሰሙ እርዷቸው” (km 7/12) እና “በምሽት አገልግሎት መካፈል ትችላላችሁ?” (km 10/12)። አድማጮች በእነዚህ ርዕሶች ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት