የካቲት 11 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 27 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 1 ከአን. 8-15 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 26-28 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ማቴዎስ 27:24-44 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአምላክ ትዕግሥት ለመዳን የሚያበቃው እንዴት ነው?—2 ጴጥ. 3:9, 15 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:- ‘ለትንቢት ከሚገባ በላይ ብዙ ትኩረት ትሰጣላችሁ’—rs ገጽ 297 አን. 5 እስከ ገጽ 298 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 6:19-21 እና ሉቃስ 16:13 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ዘገባዎች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።
20 ደቂቃ፦ “ረዳት አቅኚ ትሆናለህ?” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ የሚያቀርበው። አንቀጽ 2 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ በመጋቢት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ላቀዱ ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ፤ አንደኛው የሙሉ ቀን ሠራተኛ፣ ሌላኛው ደግሞ በጤና መቃወስ ምክንያት የአቅም ገደብ ያለበት ሊሆን ይችላል። አቅኚ ለመሆን ምን ማስተካከያ ለማድረግ አስበዋል? አንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አንድ ባልና ሚስት ወይም ልጆች ያሏቸው ባለትዳሮች ከቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ከማስፋት ጋር በተያያዘ ሊያደርጉ ያሰቡትን ነገር ለይተው በመጥቀስ ዕቅድ ሲያወጡ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 44 እና ጸሎት