የርዕስ ማውጫ ሚያዝያ 29 የሚጀምር ሳምንት
ሚያዝያ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 50 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 5 ከአን. 1-8 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 22-24 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በግንቦት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ። “የማስታወቂያ ሰሌዳውን በየጊዜው ትመለከታለህ?” የሚለውን ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ልናውጀው የሚገባ መልእክት—“ይህ የመንግሥት ወንጌል።” በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 279 አንስቶ እስከ ገጽ 281 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 16:21-23 እና ሉቃስ 9:22-26 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ጥቅሶች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 20 እና ጸሎት