የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 29, 2013 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. በማርቆስ 10:6-9 ላይ ኢየሱስ ስለ ትዳር ምን ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥቷል? [መጋ. 4, w08 2/15 ገጽ 30 አን. 8]
2. ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል ሲባል ምን ማለት ነው? (ማር. 12:30) [መጋ. 4, w97 10/15 ገጽ 13 አን. 4]
3. በማርቆስ 13:8 ላይ የተገለጸው “የምጥ ጣር” ምንድን ነው? [መጋ. 11, w08 3/15 ገጽ 12 አን. 2]
4. ሉቃስ የወንጌል ዘገባውን ሲጽፍ ያመሳከራቸው ጽሑፎች የትኞቹ ናቸው? (ሉቃስ 1:3) [መጋ. 18, w09 3/15 ገጽ 32 አን. 4]
5. ሰይጣን ታማኝነታችንን ለመፈተን “አመቺ ጊዜ” እንደሚፈልግ ማወቃችን ምን እንድናደርግ ያነሳሳናል? (ሉቃስ 4:13) [መጋ. 25, w11 1/15 ገጽ 23 አን. 10]
6. በሉቃስ 6:27, 28 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ሐሳብ ተግባራዊ ማድረግ የሚኖርብን እንዴት ነው? [መጋ. 25, w08 5/15 ገጽ 8 አን. 4]
7. ኢየሱስ፣ ራሱን ቤዛዊ መሥዋዕት አድርጎ ከማቅረቡ በፊት የአንዲትን ሴት ኃጢአት እንዴት ይቅር ሊል ቻለ? (ሉቃስ 7:37, 48) [ሚያ. 1, w10 8/15 ገጽ 6-7]
8. የክርስቶስ ተከታዮች ዘመዶቻቸውን ‘መጥላት’ ያለባቸው ከምን አንጻር ነው? (ሉቃስ 14:26) [ሚያ. 15, w08 3/15 ገጽ 32 አን. 1፤ w92 7/15 ገጽ 9 ከአን. 3-5]
9. “በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ” የሚታዩት “ምልክቶች” በሰዎች ላይ ምን ውጤት ይኖራቸዋል? (ሉቃስ 21:25) [ሚያ. 22, w97 4/1 ገጽ 15 አን. 8-9]
10. ከባድ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን በጸሎት ረገድ ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? (ሉቃስ 22:44) [ሚያ. 29, w07 8/1 ገጽ 6 አን. 2]