የማስታወቂያ ሰሌዳውን በየጊዜው ትመለከታለህ?
ሽማግሌዎች፣ የጉባኤ አገልጋዮች እና በጉባኤ ውስጥ ኃላፊነት ያለባቸው ሌሎች ወንድሞች ክፍል ወይም ኃላፊነት ያላቸው መቼ እንደሆነ ለማወቅ የማስታወቂያ ሰሌዳውን በየጊዜው ይመለከታሉ። ይሁንና ሁሉም የጉባኤው አባላት ጠቃሚ የሆነ መረጃ ከማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ ማግኘት ይችላል። የመንግሥት አዳራሹን የማጽዳት ተራህ መቼ እንደሆነ ታውቃለህ? የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ወይም ቅርንጫፍ ቢሮው ለጉባኤው የላከው አስፈላጊ ደብዳቤ አለ? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህን መጋበዝ እንድትችል በዚህ ሳምንት የሚሰጠው ሕዝብ ንግግር ርዕስ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? በስብሰባ ፕሮግራም ወይም በመስክ አገልግሎት ስምሪት ቡድንህ ላይ ለውጥ ተደርጓል? ከእነዚህ መረጃዎች መካከል አብዛኞቹ ከመድረክ መነገራቸው ቆሟል፤ እንዲሁም ሽማግሌዎች እነዚህን መረጃዎች ለአስፋፊዎች በግለሰብ ደረጃ መናገር አይችሉም። በመሆኑም የማስታወቂያ ሰሌዳውን በየጊዜው መመልከት ይኖርብናል። የማስታወቂያ ሰሌዳውን በየጊዜው የምንመለከት ከሆነ “ሁሉም ነገር በአግባብና በሥርዓት” ሊከናወን ይችላል።—1 ቆሮ. 14:40