የርዕስ ማውጫ ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት
ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 5 ከአን. 9-15 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 1-4 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዮሐንስ 3:22-36 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ‘በመንፈስ መመላለስ’ ሲባል ምን ማለት ነው?—ገላ. 5:16 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በሰማዕትነት ከሞቱት ሌሎች ሰዎች ሞት የሚለየው በምንድን ነው?—rs ገጽ 305 አን. 2 እስከ ገጽ 306 አን.2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በግንቦት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ፤ በመቀጠልም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያም በተመሳሳይ መንገድ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ። (መዝ. 127:1) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 149 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 151 አንቀጽ 1 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
መዝሙር 47 እና ጸሎት