ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ግንቦት እና ሰኔ፦ ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት፣ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? ወይም እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ በተባለው ብሮሹር ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚችል ልታሳዩት ትችላላችሁ። ሐምሌ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ወይም ሌላ ማንኛውም ብሮሹር።
◼ ጉባኤዎች የአውራጃ ስብሰባቸውን ለማድረግ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው በሚያደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ማስተካከያ በማድረግ በዚህ የመንግሥት አገልግሎት ላይ የቀረቡትን ምክሮችና ማሳሰቢያዎች መከለስ ይችላሉ። የአውራጃ ስብሰባውን ካደረጉ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል ተጠቅመው አስፋፊዎች ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆነው ባገኟቸው ሐሳቦች ላይ ውይይት ማድረግ ይችላሉ።
◼ ወደ ሌላ አገር በምትሄዱበት ወቅት እዚያ በሚካሄደው የአውራጃ ስብሰባ ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ www.pr2711.com/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ “ስለ እኛ” የሚለውን በመክፈት “የአውራጃ ስብሰባዎች” በሚለው ሥር ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።