የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ሰዎች ስንባል አንድ የሚያደርገን ነገር አለ፤ ሁላችንም ስህተት እንሠራለን። አምላክ ከባድ የሆኑ ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ይህን ርዕስ ይመልከቱ።” የግንቦት 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 15 ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ሰዎች ምን ሐሳብ እንዳላቸው እየተወያየን ነበር። [1 ዮሐንስ 4:8ን አንብብ።] ብዙ ሰዎች እዚህ ጥቅስ ላይ ባለው ሐሳብ ይስማማሉ፤ ሌሎች ደግሞ አምላክ የተፈጥሮ አደጋዎችን በማምጣቱ አሊያም እንዲህ ያሉ አደጋዎች እንዲኖሩ በመፍቀዱ ጨካኝ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት አምላክን ጨካኝ አድርገን መቁጠር የሌለብን ለምን እንደሆነ የሚገልጹ ምክንያታዊ የሆኑ ሐሳቦች ይዟል።”
ንቁ! ግንቦት
“ከጎረቤቶቻችን ጋር ብዙዎችን እያስጨነቀ ስላ አንድ ችግር ማለትም ስለ ወንጀል እየተነጋገርን ነበር። አንዳንዶች ወንጀልን ለመቆጣጠር ቁልፉ የፖሊሶችን ቁጥር መጨመር እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወንጀል ጨርሶ የሚጠፋበት ጊዜ እንደሚመጣ የሚናገር መሆኑን ያውቃሉ? [መዝሙር 37:10, 11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ይህን ጉዳይ ያብራራል፤ እንዲሁም ራሳችንን ከወንጀል ለመከላከል የትኞቹን ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ እንደምንችል ይገልጻል።”