የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በጥቅምት ወር 1,885 የዘወትር አቅኚዎች እንደነበሩ ማወቃችን ትልቅ ደስታ እንደሚፈጥርልን ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህ ላይ የልዩ አቅኚዎቹን ቁጥር ስንደምር በአገሪቱ ካሉት ጠቅላላ አስፋፊዎች አንድ አራተኛ የሚሆኑት በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ናቸው ማለት ይቻላል። ሌሎች ደግሞ በየወሩ ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለግላሉ። ይህን ግሩም የሆነ የአቅኚነት መንፈስ ይዛችሁ እንድትቀጥሉ እናበረታታችኋለን!
በተጨማሪም በተደረጉት 24 የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በጠቅላላ 17,057 የደረሰ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር መገኘቱና 297 ወንድሞችና እህቶች መጠመቃቸው በጣም የሚያበረታታ ነው።