ግንቦት 13 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 4 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 5 ከአን. 16-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 5-7 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዮሐንስ 6:22-40 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ቤዛው ኢየሱስ ባቀረበበት መንገድ መቅረቡ አስፈላጊ የሆነው ለምን ነበር?—rs ገጽ 306 አን. 4-6 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በዘኍልቍ 15:37-40 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በሰኔና በሐምሌ የምናበረክተው ጽሑፍ። በንግግር የሚቀርብ። በእነዚህ ወራት የምናበረክታቸው ትራክቶች በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት የሚስቡት ለምን እንደሆነ በአጭሩ ተናገር። ከትራክቶቹ መካከል አንዱን ወይም ሁለቱን እንዴት ከቤት ወደ ቤት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 5:11, 12 እና ማቴዎስ 11:16-19 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ዘገባዎች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ “ለመስበክ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 51 እና ጸሎት