የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 24, 2013 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. በዮሐንስ 2:20 ላይ የተጠቀሰው ‘ለመገንባት አርባ ስድስት ዓመት የፈጀው’ ቤተ መቅደስ የትኛው ነው? [ግን. 6, w08 4/15 ገጽ 30 አን. 6]
2. የክርስቶስ ተከታዮች በራሳቸው ሕይወት የሚኖራቸው ወይም የዘላለም ሕይወት የሚያገኙት መቼ ነው? (ዮሐ. 6:53) [ግን. 13, w03 9/15 ገጽ 31 አን. 3]
3. ኢየሱስ ፍጽምና ለጎደላቸው የሰው ልጆች ስለ አባቱ የገለጠው እንዴት እንደሆነ በምሳሌ አስረዳ። (ዮሐ. 8:28) [ግን. 20, w11 4/1 ገጽ 7 አን. 2]
4. ኢየሱስ ወዳጁ አልዓዛር ሲሞት ‘እንባውን ማፍሰሱ’ ምን ያስተምረናል? (ዮሐ. 11:35) [ግን. 20, w08 5/1 ገጽ 24 አን. 3-5]
5. ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ምን ከባድ ትምህርት ሰጥቷል? (ዮሐ. 13:4, 5) [ግን. 27, w99 3/1 ገጽ 31 አን. 1]
6. የአምላክ መንፈስ አካሄዳችንን አስተማማኝ በሆነ መንገድ የሚመራልን እንዴት ነው? (ዮሐ. 14:26) [ግን. 27, w11 12/15 ገጽ 14-15 አን. 9]
7. በዮሐንስ 21:15 ላይ “ከእነዚህ” የተባሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? የምናገኘው ትምህርትስ ምንድን ነው? [ሰኔ 3, w08 4/15 ገጽ 32 አን. 11]
8. በሐዋርያት ሥራ 2:44-47 እና በሐዋርያት ሥራ 4:34, 35 ላይ ባለው ዘገባ መሠረት ክርስቲያኖች ምን ዓይነት መንፈስ ማሳየት ይኖርባቸዋል? [ሰኔ 10, w08 5/15 ገጽ 30 አን. 5]
9. በሐዋርያት ሥራ 7:59 ላይ ባለው ዘገባ ላይ እስጢፋኖስ የጸለየው ለኢየሱስ ነበር? [ሰኔ 17, w08 5/15 ገጽ 31 አን. 3]
10. የበርናባስን ግሩም ምሳሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችንስ ምን ጥቅም ያስገኝልናል? (ሥራ 9:26, 27) [ሰኔ 24, bt ገጽ 65 አን. 19]