አንድ ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በማንሳት ሁለቱንም መጽሔቶች አበርክቱ
ሁለቱ መጽሔቶቻችን በርካታ ትኩረት የሚስቡ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዘው ይወጣሉ። እያንዳንዱን ቤት ስናንኳኳ ሁለቱንም መጽሔቶች ለማስተዋወቅ ስንል የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ከምናነሳ ይልቅ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ብቻ መወያየቱ የተሻለ ነው። አስተዋዮች ከሆንን እንዲሁም ከመጽሔቶቻችን ጋር በደንብ ከተዋወቅን የምናነጋግረውን ሰው ትኩረት ሊስብ የሚችል ሐሳብ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! ላይ መጥቀስ እንችላለን። ለምሳሌ ያህል፣ በቤቱ ወይም በግቢው ውስጥ የልጆች መጫወቻ ከተመለከትን ስለ ቤተሰብ የሚናገር ርዕስ መጥቀስ እንችላለን። በሩን የከፈተው ግለሰብ ወንድ ከሆነ መልካም አስተዳደርን የመሳሰሉ የወንዶችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ጉዳዮችን ማንሳት እንችላለን። ውይይት የምናደርገው በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ብቻ ቢሆንም የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ አብዛኛውን ጊዜ ሁለቱንም መጽሔቶች ማበርከታችን ተመራጭ ነው።