ሐምሌ 1 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 8 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 11-14 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 11:1-18 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የቤዛው ዝግጅት በአኗኗራችን ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያስከትል ይገባል?—rs ገጽ 310 አን. 6 እስከ ገጽ 311 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጓደኛ አድርገህ የምትመርጠው እነማንን ነው?—መዝ. 119:63 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ፤ በመቀጠልም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያም በተመሳሳይ መንገድ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤ እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ሉቃስ 12:16-31 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 35 እና ጸሎት