ሐምሌ 22 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 9 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 22-25 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 22:17-30 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የምንኖረው በዓለም ውስጥ ቢሆንም የዓለም ክፍል እንዳልሆንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—ዮሐ. 17:15, 16 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ከነሥጋዊ አካላቸው ወደ ሰማይ ሊወሰዱ ይችላሉ?—rs ገጽ 313 አን. 2-3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ተዘጋጅታችኋል? በውይይት የሚቀርብ። ክርስቲያን ወጣቶች በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች መቋቋም እንዲችሉ ከወዲሁ ለማዘጋጀት በቤተሰብ አምልኮ ወቅት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫን፣ የወጣቶች ጥያቄ የተባሉትን መጻሕፍት፣ ድረ ገጻችንንና ሌሎች ቲኦክራሲያዊ መሣሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ግለጽ። (1 ጴጥ. 3:15) ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ወይም ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን ምረጥና በዚያ ዙሪያ ከጽሑፎቻችን ያገኘሃቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ተናገር። ተማሪዎች በነበሩበት ወቅት በትምህርት ቤት ውስጥ ምሥክርነቱን መስጠት የቻሉት እንዴት እንደነበር እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ “ውጤት የሚያስገኝ ዘመቻ።” በሚያዝያ 2013 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 1 እና ጸሎት