ሐምሌ 29 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 9 ከአን. 10-16 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 26-28 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 26:19-32 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ታማኝ ክርስቲያኖች ሳይሞቱ በሚስጥር ወደ ሰማይ ይወሰዳሉ?—rs ገጽ 313 አን. 4 እስከ ገጽ 314 አን. 3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንፈስ በአገልጋዮቹ ላይ የሚገለጠው በምን መንገዶች ነው?—ገላ. 5:22, 23፤ ራእይ 22:17 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ስትሰብኩ የራሳችሁን ተፈጥሯዊ አነጋገር ተጠቀሙ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 128 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 129 አንቀጽ 1 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ዓይን አፋርነትን ላሸነፈ ተሞክሮ ያለው አንድ አስፋፊ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግ። አገልግሎት ሲወጣ ይሰማው የነበረውን ፍርሃት መቀነስ የቻለው እንዴት ነው?
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። አንድ ሽማግሌ በውይይት የሚያቀርበው።
10 ደቂቃ፦ የአባታችሁ ልጆች መሆናችሁን አሳዩ። (ማቴ. 5:43-45) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 89 አንቀጽ 3 እስከ ገጽ 90 አንቀጽ 1 እና በገጽ 164 አንቀጽ 2 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
መዝሙር 19 እና ጸሎት