ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 9 ከአን. 17-21 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮም 1-4 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሮም 3:21–4:8 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ራሳቸውን እንደ “መጻተኞችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች” የሚቆጥሩት ለምንድን ነው?—1 ጴጥ. 2:11፤ 1 ዮሐ. 2:15-17 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በታላቁ መከራ ጊዜ ለእውነተኛ ክርስቲያኖች ምን ጥበቃ ይደረግላቸዋል?—rs ገጽ 314 አን. 4 እስከ ገጽ 315 አን. 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በነሐሴ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ፤ በመቀጠልም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያም በተመሳሳይ መንገድ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “የ2013 የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች።” በሚያዝያ 2013 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ባለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ሉቃስ 5:27-32 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ዘገባው ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 13 እና ጸሎት