ጥቅምት 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 32 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 13 ከአን. 1-8 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ከፊልጵስዩስ 1-4 እስከ ቆላስይስ 1-4 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ከፊልጵስዩስ 3:17 እስከ 4:9 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የወላጆችን ሃይማኖት መተው ትክክል ነው?—rs ገጽ 323 አን. 2-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጸሎት ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚረዳን እንዴት ነው?—ሉቃስ 11:9-13፤ ያዕ. 1:5 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ዓለም አቀፋዊ አንድነታችን ይሖዋን ያስከብረዋል። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 165 አንቀጽ 2 አንስቶ በገጽ 168 ላይ እስከሚገኘው ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አንድነታችንና ፍቅራችን ለሰዎች ምሥክርነት ለመስጠት እንዳስቻለ የሚያሳዩ በጽሑፎች ላይ የወጡ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ አንዳንድ አድማጮችን ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “የመንግሥት ዜና ቁጥር 38 በኅዳር ወር ይሰራጫል!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመንግሥት ዜና ቁጥር 38 አንድ ቅጂ ለሁሉም አድማጮች እንዲታደል አድርግ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የጉባኤውን ክልል ለመሸፈን ስለተደረገው ዝግጅት እንዲናገር ጋብዝ። በገጽ 4 ላይ የቀረበውን አጭር የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም የመንግሥት ዜናው ሲበረከት የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 53 እና ጸሎት