ጥቅምት 28 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 13 ከአን. 18-21 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ጢሞቴዎስ 1 እስከ 2 ጢሞቴዎስ 4 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ “በበዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ?” በንግግር የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ የምሥራቹን ጠቀሜታ ጎላ አድርጋችሁ ግለጹ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 158 አንቀጽ 5 እስከ ገጽ 159 መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት የሚስብ ሐሳብ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ ሰዓት የማክበር አስፈላጊነት። በውይይት የሚቀርብ። (1) ይሖዋ ጊዜን በመጠበቅ ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ዕን. 2:3) (2) በስብሰባዎችና በአገልግሎት ላይ በሰዓቱ መገኘት ለይሖዋ አክብሮት እንዳለንና ለሌሎች አሳቢ እንደሆንን የሚያሳየው እንዴት ነው? (3) የመስክ አገልግሎት ስብሰባ ላይ ማርፈዳችን በመስክ አገልግሎት ቡድኑና ስምሪቱን በሚመራው ወንድም ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? (4) ፍላጎት ላሳየ ሰው ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን በሆነ ሰዓት ላይ እንደምንመጣ ከተናገርን ቀጠሯችንን ማክበራችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ማቴ. 5:37) (5) በአገልግሎትም ሆነ በጉባኤ ስብሰባ ላይ በሰዓቱ ለመገኘት አስቀድመን ምን ማድረግ እንችላለን?
መዝሙር 11 እና ጸሎት