በበዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ?
ብዙ ሰዎች በሃይማኖታዊና በብሔራዊ በዓላት ቀን ሥራ ስለሌላቸው ቤታቸው ይገኛሉ፤ በመሆኑም እነዚህ ቀናት በአገልግሎት ለመካፈል ጥሩ አጋጣሚ ይከፍቱልናል። ጉባኤዎች በበዓል ቀን ለመመሥከር ልዩ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። በክልላችን ያሉ ብዙ ሰዎች ከእንቅልፋቸው የሚነሱት አርፍደው ከሆነ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባው በሚጀመርበት ሰዓት ላይ ማስተካከያ ማድረግ ጥሩ ሊሆን ይችላል። በበዓል ቀን ለመመሥከር የተደረገ ልዩ ዝግጅት ሲኖር ሁሉም አስፋፊዎች እንዲገኙ ለማበረታታት ይህን ዝግጅት በተመለከተ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ማስታወቂያ ሊነገር ይችላል። እርግጥ ነው፣ በበዓል ቀን ለማረፍና የራሳችንን ጉዳዮች ለማከናወን እንፈልግ ይሆናል። ያም ሆኖ የተወሰነውን ጊዜ ለምን ለአገልግሎት አናውለውም? እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ በቅዱስ አገልግሎት መካፈል የሚያስገኘውን ደስታ ማጣጣም ትችላላችሁ።—ማቴ. 11:29, 30